የኦፌኮ የአዲስ አበባ ቢሮ በወታደሮች ተወረረ -መረራ ጉዲና ቢሮ አልነበሩም

በዛሬው የክብ ጠረጴዛ ውሎዋ ሚሚ ስብሐቱ በኦሮሚያ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን ተቃውሞ በገንዘብና በቁሳቁስ በውጪ የሚገኙ ኃይሎች እንደሚረዱ ይህንን እርዳታም በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተመዘገቡ ፓርቲዎች ህጋዊነታቸውን ከለላ በማድረግ ገንዘቡንና ቁሳቁሱን እንደሚያከፋፍሉ ገልፃ ነበር ።

ከነበረኝ ልምድ በመነሳትም የሚሚን ቱልቱላ ተከትሎ አንድ ፓርቲ ኢላማ እንደሚሆን እየጠበቅሁ ነበር ።ጥበቃዬ ብዙ ሳይቆይ የፕሮፌሰር መረራ ኦፌኮ በድጋሚ የስርዓቱ ጡጫ ሊያርፍበት መንገድ መጀመሩን የሚያሳይ ዜና ተገኝቷል ።
የኦሮሚያውን ተቃውሞ ተከትሎ ኦፌኮ ብዙ ዋጋ ከፍሏል ።አባላቱ ተገድለውበት አመራሮቹ እነበቀለ ገርባ ወህኒ ወርደውበታል።
ዛሬ ደግሞ ሸገር የሚገኘው ዋና ቢሮው በወታደሮች ተወርሮ ፅህፈት ቤቱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ድብደባ ተፈፅሞባቸው ተወስደዋል ።መረራ ጉዲና በቢሮው አለመኖራቸው ቢታወቅም በቀጣይ ምን ሊደረግ እንደሚችል አይታወቅም ።

Dawit Solomon Yemesgen's photo.

ሽመልስ ከማልና ፈትያ የሱፍ በፕሬስ ድርጅት እየተወዛገቡ ነው

‹ችግሮች በአስቸኳይ ካልተፈቱ ለበላይ አካል እናሳውቃለን›› ፈትያ የሱፍ
‹‹ችግሮቹ ውጫዊ ናቸው›› አቶ ሽመልስ ከማል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዙሪያ እየተወዛገቡ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል የፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ ላለፉት አራት አመታት ድርጅቱ በተለያዩ ችግሮች ተዘፍቆ እያለ በቦርድ ሰብሳቢነታቸው ችግሮቹን መፍታት የነበረባቸው ቢሆንም ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎችን ችላ በማለት ድርጅቱ ከእነ ችግሮቹ እንዲዘልቅ አድርገዋል በማለት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ ተናግረዋል፡፡ ሰሞኑን የ2007 የበጀት እቅድን ለመገምገም በተገናኙበት ወቅት የፕሬስ ድርጅት ቦርድ እና አስተዳደር በበርካታ ችግሮች ዙሪያ ወቀሳ እንደደረሰበትና ችግሮቹ እንዲፈቱም ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ በራሱ ድርጅት እየታተመ የሚወጣው ኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ በቅዳሜ እትሙ አስነብቧል፡፡

በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር ብልሹነት መኖሩን የተናገሩት ፈትያ የሱፍ፣ ‹‹በራሱ ድርጅት በችግር የተተበተበ ጋዜጠኛ እንደምን የሌሎችን ድርጅቶችና ግለሰቦች የአሰራር ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አክለውም በተደጋጋሚ ችግሮቹ ለድርጅቱ አስተዳደር በሰራተኞች ሲቀርቡለት የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ እያለ ማለፉን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ አውስተዋል፡፡

ፈትያ የሱፍ እንደሚሉት የፕሬስ ድርጅት ቦርድ እና አስተዳደር ችግሮቹን በአስቸኳይ የማይፈታ ከሆነ ወደሚመለከተው ከፍተኛ አካል ለማስተላለፍ ከውሳኔ ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡

የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል በበኩላቸው የድርጅቱ ችግሮች ውጫዊ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ድርጅቱ የበጀት ችግሮች እንዳለበት ያወሱት አቶ ሽመልስ፣ በተጨማሪ ግን በድርጅቱ ላይ መጥፎ እይታ ያላቸው እና መጠቀሚያ ለማድረግ የሚፈልጉ አካላት በሰራተኞች ስም አላማቸውን ለማስፈጸም የሚሯሯጡ ወገኖች አሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‹‹የግል እና የመንግስት ሚዲያ ይለያያሉ፤ በአመለካከት፣ በአሰራርና በጥራት ልዩነት አላቸው›› በማለትም ሰራተኞቹ ፕሬስ ድርጅት እንደ ግል ሚዲያ ሊሰራ እንደማይችል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደ እና አቶ ሽመልስ ከማል ከፍተኛ የሆነ የጥቅም ትስስሮሽ እንዳላቸው የሚገልጹት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች፣ በዚህ ትስስራቸው የተነሳም የአቶ ሽመልስ ከማል ባለቤት ያለምንም ውድድር በድርጅቱ በጋዜጠኝነት ተቀጥራ ምንም ስራ ሳትሰራ ደመወዝ ትወስድ እንደነበር፣ በኋላ ግን ‹ስራውን አልቻልኩትም› በሚል ከድርጅቱ እንደወረጣች ይናገራሉ፡፡

አቶ ሰብስቤ ከበደ በሰራተኞች ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው እና በተለያዩ ስብሰባዎች በይፋ ‹አልቻልክም ድርጅቱን ልቀቅ› ተብለው በሰራተኞች እንደተነገራቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን ከአቶ ሽመልስ ከማል ጋር ባለቸው የጥቅም ትስስር በስልጣናቸው እስካሁን እንደሚገኙ፣ ይህም ድርጅቱን እና ሰራተኞችን እየጎዳ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኢህአዴግ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ታወቀ

የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጥሯል

ገዥው ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ለማሰር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ታማኝ ምንጮች ገለጹ፡፡ ሰሞኑን የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባደረጉት ስብሰባ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃልን ወይንስ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን ማሰር ያዋጣል በሚል ልዩነት እንደተፈጠረ የገለጹት ምንጮቻችን በስተመጨረሻም የኢንጅነር ይልቃል መታሰር ትኩረት የሚስብ በመሆኑ ንቁ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን ማሰር አዋጭ ነው የሚለው ቡድን ተደማጭነት እንዳገኘ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የሰማያዊና ሌሎች ፓርቲዎች አመራሮችን ‹‹ከኢሳት ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ›› በሚል በሽብር ስም ለመክሰስ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችንም ሆነ ሌሎችን ‹‹ከኢሳት ጋር ግንኙነት አላቸው›› በሚል ይከሰሳሉ የተባሉት እስከህዳር ወር መጨረሻ ሊታሰሩ ይችላሉ ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በዚሁ ስብሰባ ኢንጅነር ይልቃል ወይንም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን በማሰር ከተፈጠረው ልዩነት በተጨማሪ አመራሮችን በተለያዩ ሰበቦች ለማሰር በተዘጋጀውና ‹‹በዚህ መንገድ መሄዱ እስከመቼ ያዋጣናል?›› የሚሉ ጥያቄ በሚያነሱ ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች ልዩነት መፈጠሩንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር በሌሎች የፓርቲው አካሄዶች ላይ ልዩነት በመፈጠሩ ፓርቲው ውስጥ አደጋ ተፈጥሯል ያሉት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች በአቶ አባይ ፀሐዬ የሚመራ ቡድን ‹‹ልዩነታችን ቢያንስ እስከ ምርጫው ድረስ ማቻቻል አለብን›› በሚል በሁለቱ ቡድን መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት እየጣረ ነው ብለዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች 8 ፓርቲዎች ጋር በመተባበር የአዳር ሰልፍን ጨምሮ የአንድ ወር መርሃ ግብር ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን የወሩ የመጀመሪያ መርሃ ግብር የሆነው የአደባባይ ስብሰባ ለማድረግ ሲቀሰቅሱ የተገኙ የፓርቲው አራት አመራሮች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡

በተከሰሱ መፅሄቶች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ፍ/ቤት ኦሪጂናል መፅሄቶች እንዲቀርቡለት አዘዘ

በ“አዲስ ጉዳይ”፣ በ“ሎሚ” እና በ“ፋክት” መፅሄት አሳታሚዎችና ሥራ አስኪጆች ላይ ለተመሰረቱት የወንጀል ክሶች የቀረቡት ማስረጃዎች ከየመፅሄቶቹ ገፆች የተቆራረጡና ኮፒ የተደረጉ መሆናቸውን የጠቆመው ፍ/ቤት፤ አቃቤ ህግ ኦርጂናል መፅሄቶችን በማስረጃነት እንዲያቀርብ ትዕዛዝ በማስተላለፍ ለፍርድ ውሳኔ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ፡፡ ፍ/ቤቱ ከትላንት በስቲያ በዋለው ችሎት አቃቤ ህግ ከጥቅምት 3 በፊት ኦሪጂናል መፅሄቶችን በማስረጃነት እንዲያቀርብ አዟል፡፡ የ“አዲስ ጉዳይ” መፅሄት አሳታሚ ሮዝ አሳታሚና ስራ አስኪያጁ አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ፣ የ“ሎሚ” መፅሄት አሳታሚ ዳዲሞስ ኢንተርቴይመንትና ፕሬስ ስራዎችና ስራ አስኪያጁ አቶ ግዛው ታዬ እንዲሁም የ“ፋክት” መፅሄት አሳታሚ ኢንተርቴይመንትና የፕሬስ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበርና ስራ አስኪያጅ ፋጡማ ኑርዬ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት ታትመው በወጡ መፅሄቶቻቸው ሃሰተኛ ወሬዎች በማውራት፣ ለአመፅ የሚያነሳሱ ፅሁፎችን ለህዝብ በማድረስ፣ በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ስርአቱ ላይ አመፅ ለማስነሳት ሞክረዋል የሚሉ ክሶች እንደቀረበባቸው ይታወሳል፡፡ ከ“ፋክት” መፅሄት አሳታሚ ድርጅት ስራ አስኪያጅ በስተቀር የሁሉም ተከሳሽ መፅሄቶች ሥራ አስኪያጆችና ባለቤቶች አገር ለቀው መውጣታቸው ይታወቃል፡፡

ጥበቡ ወርቅዬ ወደ ሙዚቃው አለም ሊመለስ ነው!

በ 1990ዎቹ አጋማሽ በለቀቀው አልበም የሙዚቃውን ኢንደስትሪው በዝና የተቀላቀለው አርቲስት ጥበቡ ወርቅዬ ሙዚቃ አቁሜያለው ካለ ከአጭር ጊዜ በኋላ ወደ ሙዚቃው ኢንደስትሪ ሊመለስ መሆኑን የቅርብ ምንጮች ይፋ አድርገዋል.

አርቲስቱ በ1990ዎቹ አጋማሽ ባወጣው የዘላለሜ ነሽ አልበም ከፍተኛ ዝናን አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ከዛ ዘመን በኋላ በተለይም የሸዋንዳኝ ኃይሉ እና ዘሪቱ ከበደ አልበሞች ከወጡ በኋላ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ የመጣው አብዮት ምቾት ካልሰጣቸው በርካታ ምርጥ ድምጻዊያን አንዱ ነበር። ጥበቡ ወርቅዮ ኢንተርቴይንመት በሚልም የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት ከፍቶ ነበር። ሆኖም በሙዚቃው እንደስትሪ ላይ የተፈጠረው ቁልቁል መውረድ እና የቅጅ መብት መጣስ ችግር አርቲስቱን እንዳበሳጨው የቅርብ ምንጮች አወርተዋል። ይባስ ብሎ በቅርቡም ጠቅላለውን ከሙዚቃ አለም መሰናበቱን በአንድ የቴሌቪዥን ሾው ላይ ቀርቦ ተናግሯል ተብሎ ተዘገቧል።

ይሁን እንጂ ሰሞኑን የአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች እንደሚሉት ተወዳጁ ድምጻዊ ድንገቴ በሆነ አመላለስ ወደ ሙዚቃው ኢንደስትሪ ይመለሳል። {እንዴት እርግጠኛ ሆናቹ ?, እራሱ አርቲስቱ በቅርቡ የመመለሱን ጉዳይ ለቅርብ ሰዎቹ ሲያወራ ተሰምቷል ብለዋል።

ድምጻዊት እናና ዱባለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አምስቱ እርጎዬዎች በመባል የሚታወቁት ድምጻዊያን አባል የነበረችው አርቲስት እናና ዱባለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ድምጻዊት እናና ከእናቷ ከወይዘሮ እርጎዬ ጸጋው እና ከአባቷ አቶ ዱባለ ታርፋለህ በ1971 ዓ.ም ነበር በጎንደር አዘዞ ከተማ የተወለደችው።
በስምንት ዓመት ዕድሜዋ ወደ አዲስ አበባ የመጣችው እናና ከእህቶቿ ጋር ልዩ ስሙ ግቢ ገብርኤል በሚባለው አካባቢ መኖር እንደጀመረችና በለጋ
እድሜዋ ሙዚቃ መጀመሯን እህቷ የሺመቤት ዱባለ ተናግራለች። ድምጻዊቷ በ1982 ዓ.ም አምስቱ እርጎዬዎች በሚል ስያሜ ከሚጠሩት
እህቶቿ ጋር ባወጣችው የሙዚቃ ካሴት በተለይም ”ጭር ሲል አልወድም”በሚለው ዜማዋ ትታወቃለች።
እናና ከእህቶቿ ጋር ሶስት፣ ለብቻዋ ሁለት ሙሉ ካሴት ያሳተመች ሲሆን ከድምጻዊ አበበ ፈቃደ ጋር በሁለት የሙዚቃ ስብስቦች በቅብብሎሽ
ያቀረበቻቸው ዜማዎቿ በሕዝብ ዘንድ ዝናን አትርፈውላታል።
በቅርቡ የሙዚቃ ካሴት ለማውጣት በዝግጅት ላይ እንደነበረችም እህቷ የሺመቤት ዱባለ ገልፃለች።
አርቲስቷ ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም በቤተዛታ ሆስፒታል በሕክምና ስትረዳ ቆይታ ነው ትናንት ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው።
የቀብሯ ሥነ-ሥርዓት ነገ ነሐሴ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ ስድስት ሠዓት ቤተሰቦቿ፣ ወዳጅ ዘመዶቿና የሙያ አጋሮቿ በተገኙበት ጉርድ ሾላ
በሚገኘው ሳሊተ ምህረት ማርያም ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

ድምጻዊት እናና ዱባለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

አምስቱ እርጎዬዎች በመባል የሚታወቁት ድምጻዊያን አባል የነበረችው

አርቲስት እናና ዱባለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ድምጻዊት እናና ከእናቷ ከወይዘሮ እርጎዬ ጸጋው እና ከአባቷ አቶ ዱባለ

ታርፋለህ በ1971 ዓ.ም ነበር በጎንደር አዘዞ ከተማ የተወለደችው።

በስምንት ዓመት ዕድሜዋ ወደ አዲስ አበባ የመጣችው እናና ከእህቶቿ ጋር

ልዩ ስሙ ግቢ ገብርኤል በሚባለው አካባቢ መኖር እንደጀመረችና በለጋ

እድሜዋ ሙዚቃ መጀመሯን እህቷ የሺመቤት ዱባለ ተናግራለች።

ድምጻዊቷ በ1982 ዓ.ም አምስቱ እርጎዬዎች በሚል ስያሜ ከሚጠሩት

እህቶቿ ጋር ባወጣችው የሙዚቃ ካሴት በተለይም ”ጭር ሲል አልወድም”

በሚለው ዜማዋ ትታወቃለች።

እናና ከእህቶቿ ጋር ሶስት፣ ለብቻዋ ሁለት ሙሉ ካሴት ያሳተመች ሲሆን

ከድምጻዊ አበበ ፈቃደ ጋር በሁለት የሙዚቃ ስብስቦች በቅብብሎሽ

ያቀረበቻቸው ዜማዎቿ በሕዝብ ዘንድ ዝናን አትርፈውላታል።

በቅርቡ የሙዚቃ ካሴት ለማውጣት በዝግጅት ላይ እንደነበረችም እህቷ

የሺመቤት ዱባለ ገልፃለች።

አርቲስቷ ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም በቤተዛታ ሆስፒታል በሕክምና

ስትረዳ ቆይታ ነው ትናንት ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው።

የቀብሯ ሥነ-ሥርዓት ነገ ነሐሴ 11 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ ስድስት ሠዓት

ቤተሰቦቿ፣ ወዳጅ ዘመዶቿና የሙያ አጋሮቿ በተገኙበት ጉርድ ሾላ

በሚገኘው ሳሊተ ምህረት ማርያም ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።” width=”179″ height=”172″ />

<div class=

ለጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላ የተፈቀደው ዋስትና ተከለከለ

ከአሸናፊ ደምሴaziza ena weyeneshet

በአንዋር መስጊድና አካባቢው ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በተፈጠረ ግጭትና ሁከት ተሳትፈዋል በሚል ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው ከሚገኙ 14 ተጠርጣሪዎች መካከል ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ለሦስት ሰዎች ፍርድ ቤት ትናንት ጠዋት ፈቅዶት የነበረው የ5 ሺህ ብር የዋስትና መብት ከሰዓት በኋላ በፖሊስ በቀረበ ይግባኝ ውድቅ ሆኖ ዋስትናው ተከለከለ።
ሜክስኮ በሚገኘው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዮች የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ማስቻያ ችሎት የዛሬ ሳምንት የተሰጣቸውን የጊዜ ቀጠሮ ተከትሎ በችሎት ካቀረቡት 14 ተጠርጣሪዎች መካከል የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛዋ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችውን ወ/ት ወይንሸት ሞላን ጨምሮ አራት የፖሊስ አባላት (ማለትም አንድ ኢንስፔክተር፣ አንድ ምክትል ኢንስፔክተርና አንድ ምክትል ሳጅንና አንድ የኮንስታብል ማዕረግ ያላቸው) እና ሌሎች ስምንት ተጠርጣሪዎች በችሎች ሲያቀርብ የተቀሩት ከሁለተኛው የጊዜ ቀጠሮ በኋላ ፖሊስ ምርመራዬን ጨርሼባቸዋለሁ ሲል ማሰናበቱን ለፍርድ ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።
አሁን ድረስ በምርመራ ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪዎች ጠበቃ ያልቆመላቸው ሲሆን፤ በትናንት ጠዋቱ የችሎት ውሏቸውም በባለፈው የጊዜ ቀጠሮ ወቅት ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄያቸው መሠረት ፍርድ ቤቱ፤ አዚዛ መሐመድ፣ ወይንሸት ሞላ እና ኡዝታዝ መንሱር የ5 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲሄዱ ትዕዛዝ ቢሰጥም፤ በቀደመው ችሎት ያቀረባቸውንና ምላሽ ያላቀረበባቸውን የዋስትና መቃወሚያዎች ፖሊስ ለችሎቱ አቅርቦ አስረድቷል። ይኸውም ምርመራዬን አልጨረስኩምና ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም፤ በሕክምና ላይ ያሉና ጉዳት የደረሰባቸውን የፖሊስ አባላትንም መጨረሻ ማወቅ ያስፈልጋል በሚል ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ይግባኝ መሠረት ችሎቱ ጠዋት ላይ የተፈቀደ ዋስትና በከሰዓት ላይ ውድቅ ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማረፊያ እንዲመለሱ ተደርጓል።
የምርመራ ተግባራቶቼን አላገባደድኩም ሲል ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮን የጠየቀው ፖሊስ በጥቁር አንበሳ እና በፖሊስ ሆስፒታል የሚገኙትንና በብጥብጡ ወቅት ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉትን ሰዎች ሁኔታና ቃል ተቀብሎ ለማቅረብ ፍርድ ቤቱን በጠየቀው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ የተፈቀደለት ሲሆን፤ ለመጪው ነሐሴ 7 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ወጣቱ ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ እስር ቤት ውስጥ እንደተደበደበ ለፍርድ ቤት ተናገረ

Abrham-Desta

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመቀሌ በሚጽፋው ጽሁፎችና በሚሰጣቸው አስተያየቶች የበርካታ ወጣቶችን ቀልብ የሳበው የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር አብርሃ ደስታ፣ በአሸባሪነት ተከሶ መእከላዊ እስር ቤት ከገባ በሁዋላ ፖሊስ ፍድር ቤት ያቀረበው ሲሆን፣ አብርሃ በፖሊሶች መደብደቡን፣ እርሱ ያልጻፋቸውን ጽሁፎች
የራሱ ጽሁፎች እንደሆኑ አድርጎ እንዲፈርም መገደዱን፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ ብቻውን እንዲቀመጥ መደረጉን እንዲሁም ፖሊሶች ያልሆኑ ሰዎች ምርምራ እንደሚያካሂዱበት ተናግሯል። በውጭ ከሚጠባበቁ አድናቂዎችና ደጋፊዎች ከፍተኛ አቀባበል የተደረገለት አብርሃም፣ በቤተሰብ እንዳይጎበኝ መደረጉንም ገልጿል።
ፍርድ ቤቱ በዘመድ እንዲጠየቅና አደጋ እንዳይደርስበት ለፖሊስ ትእዛዝ ሰጥቶ ፖሊስ ያቀረበውን የ28 ቀናት የተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። በተመሳሳይ መንገድ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክልት ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ አንድንት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌውና የድርጅቱ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሽበሺ ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።
የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ወጣት ጸሃፊዎችንና ፖለቲከኞችን በሽብርተኝነት እየከሰሱ በማሰር ላይ ናቸው። እስረኞቹ የራሳቸው ባልሆነ ጽሁፍ ላይ እንዲፈርሙ እየተገደዱ መሆናቸውን እየገለጹ ነው። ድርጊቱ በመንግስት ላይ አለማቀፍ ውግዘት እያስከተለበትም ነው። አምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግስትን ህገወጥ እርምጃ ከመጪው ምርጫ ጋር አያይዞ፣ ጋዜጠኞች፣ ጸሃፊዎችና ፖለቲካኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል። ታዋቂ አለማቀፍ የሚዲያ ተቋማትም በተመሳሳይ መንገድ በአንድ ድምጽ እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

41 አለማቀፍ ድርጅቶች የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ጠየቁ

41 አለማቀፍ ድርጅቶች የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ጠየቁ

የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ ይሻሻል ብለዋል
ከዚህ በፊት በሽብርተኝነት የተፈረደባቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል
41 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የፕሬስ ነጻነት አቀንቃኞች፣ አለማቀፍና ክልላዊ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትና የሙያ ማህበራት መንግስት በቅርቡ የሽብርተኝነት ክስ የመሰረተባቸውን ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከትናንት በስቲያ በላኩት ደብዳቤ መጠየቃቸውን ብሉምበርግ ኒውስ ዘገበ፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ አርቲክል 19 ምስራቅ አፍሪካ፣ ሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ፣ ወርልድ አሊያንስ ፎር ሲቲዝን ፓርቲሲፔሽን፣ ፔን አሜሪካና የመሳሰሉት አለማቀፍ ድርጅቶች በጋራ በጻፉት ደብዳቤ፣ መንግስት ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን በሽብርተኝነት እየከሰሰ ለእስር መዳረጉን መቀጠሉ ያሳስበናል፣ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ መገታት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ሶስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማርያን ሶስት ወራት ለሚሆን ጊዜ ይህ ነው የሚባል ክስ ሳይመሰረትባቸው ያለአግባብ በእስር ላይ መቆየታቸውንና አንዳንዶቹም በምርመራ ወቅት እንግልት እንደደረሰባቸው መናገራቸውን የጠቀሰው ደብዳቤው፣ ይህም አግባብ አለመሆኑን ገልጿል፡፡
ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ በተመሰረተባቸው የሽብርተኝነት ክስ በረጅም አመታት እስር ብሎም በሞት ሊቀጡ እንደሚችሉ ስጋታቸውን የገለጹት ድርጅቶቹ፤ ይህም አለማቀፍ ህጎችን የሚጥስና በቀጠናው የተረጋጋ ሰላምና ደህንነት ለመፍጠር የሚደረገውን አለማቀፍ ጥረት ዋጋ የሚያሳጣ እርምጃ ይሆናል ብለዋል፡፡
መንግስት አግባብነት በሌለው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ በቁጥጥር ውስጥ አውሎ ክስ የመሰረተባቸውን ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቅ አስፈላጊውን ሁኔታ እንዲያመቻቹ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ጥያቄ ያቀረቡት እነዚህ ድርጅቶች፤ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በጸረ ሽብር ህጉ ተከሰው የተፈረደባቸው ዜጎች ጉዳይ አግባብ አለመሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሳይቀር እንዳመነበትና እንዳወገዘው አስታውሰዋል፡፡
ከጋዜጠኞቹና ከጦማርያኑ በተጨማሪም፣ ከዚህ በፊት በሽብርተኝነት ተከሰውና ተፈርዶባቸው ያለአግባብ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ መንግስት በአፋጣኝ እንዲፈታና የጸረ ሽብርተኝነት ህጉንም አለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መስፈርቶችን በሚያሟላ መልኩ እንደገና አሻሽሎ እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፡፡ኢትዮጵያ የአለማቀፉ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነትና የአፍሪካን የሰብዓዊና የህዝብ መብቶች ኮንቬንሽን ፈርማ የተቀበለች ሃገር እንደመሆኗ፣  መንግስት አለማቀፍ ህጎች የጣሉበትን ግዴታ በማክበር መሰረታዊ መብቶቻቸው ተጥሰው ለእስር የተዳረጉ ዜጎችን በሙሉ ከእስር እንዲለቅ ጠይቀዋል፡፡
ደብዳቤውን የጻፉት ድርጅቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. Amnesty International
2. ARTICLE 19 Eastern Africa
3. Central Africa Human Rights Defenders Network (REDHAC), Central Africa
4. CIVICUS: World Alliance for Citizen Participation
5. Civil Rights Defenders, Sweden
6. Coalition pour le Développement et la Réhabilitation Sociale (CODR UBUNTU), Burundi
7. Committee to Protect Journalists
8. Community Empowerment for Progress Organization (CEPO), South Sudan
9. Conscience International (CI), The Gambia
10. East and Horn of Africa Human Rights Defenders Project
11. Egyptian Democratic Association, Egypt
12. Electronic Frontier Foundation
13. Ethiopian Human Rights Project (EHRP)
14. Elma7rosa Network, Egypt  15. English PEN
16. Freedom Now
17. Front Line Defenders, Dublin  18. Human Rights Watch
19. International Women’s Media Foundation (IWMF)
20. Ligue des Droits de la personne dans la region des Grands Lacs (LDGL), Great Lakes
21. Ligue Iteka, Burundi
22. Maranatha Hope, Nigeria
23. Media Legal Defence Initiative
24. National Civic Forum, Sudan
25. National Coalition of Human Rights Defenders, Kenya
26. Niger Delta Women’s movement for Peace and Development, Nigeria
27. Nigeria Network of NGOs, Nigeria
28. Paradigm Initiative Nigeria, Nigeria
29. PEN American Center  30. PEN International
31. Réseau africain des journalistes sur la sécurité humaine et la paix (Rajosep), Togo
32. Sexual Minorities Uganda (SMUG), Uganda
33. South Sudan Human Rights Defenders Network (SSHRDN), South Sudan
34. South Sudan Law Society, South Sudan
35. Tanzania Human Rights Defenders Coalition, Tanzania
36. Twerwaneho Listeners Club (TLC), Uganda
37. Union de Jeunes pour la Paix et le Développement, Burundi
38. WAN-IFRA (The World Association of Newspapers and News Publishers)
39. West African Human Rights Defenders Network (ROADDH/ WAHRDN), West Africa
40. Zambia Council for Social Development (ZCSD), Zambia
41. Zimbabwe Human Rights NGO Forum, Zimbabwe

‹ዶክተር ኢንጂነር› ሳሙኤል ዘሚካኤል ከሃገር ውጭ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ

ዶክተር ኢንጂነር› ሳሙኤል ዘሚካኤል ከሃገር ውጭ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ
– ዛሬ ማታ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ይጠበቃል
የማይገባቸውን የትምህርት ደረጃና ማዕረግ ለራሳቸው ሰጥተው ያለአግባብ ጥቅም ሲያገኙ ቆይተዋል በሚል ሲብጠለጠሉ የቆዩት ‹ዶክተር ኢንጂነር› ሳሙኤል ዘሚካኤል በሚገኙበት ኬንያ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንደዋሉና ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል፡፡
ግለሰቡ አደረጉት የተባለው ጉዳይ በመገናኛ ብዙሃንና በማኅበራዊ ድረገፆች ከተነሳ በኋላ በተለያየ መንገድ ገንዘብ ተጭበርብረናል ያሉ ሰዎች ክሳቸውን አቅርበው ለፖሊስ ቃል ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ አቶ ሳሙኤል መረጃዎቹ መነገር ከጀመሩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ወደ ኬንያ ተጉዘው የነበረ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፌደራል ፖሊስ የኢንተርፖል ቡድን እና ከኬንያ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ከቀናት በፊት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አድርጓል፡፡
የኢትዮጲካሊንክ ምንጮች እንደገለፁት ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ወደ ሃገር ቤት የሚመጡበት ሂደት ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የተጠርጣሪውን ጉዳይ ለማስፈፀምና ወደ አዲስ አበባ ይዞ ለመምጣትም አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራር አባል ወደ ናይሮቢ እንደሄዱ ተነግሯል፡፡